Numbers 15

ተጨማሪ ቍርባን

1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘እንድትኖሩበት ወደምሰጣችሁ ምድር ከገባችሁ በኋላ፣ 3ስእለታችሁን ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማድረግ ወይም በተወሰኑ በዓሎቻችሁ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ከላም ወይም ከበግ መንጋ በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ስታቀርቡ 4መሥዋዕቱን ይዞ የሚመጣው ሰው በኢን
ሁለት ሊትር ያህል ነው።
አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የኢፍ
አንድ ሊትር ያህል ነው።
አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቀርባል።
5ለሚቃጠል ወይም ለዕርድ መሥዋዕት ከሚቀርብ ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ የመጠጥ ቍርባን አብራችሁ አዘጋጁ።

6“ ‘ከአውራ በግ ጋር በኢን
አራት ተኩል ሊትር ያህል ነው።
ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ
አንድ ሊትር ያህል ነው።
ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤
7እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የኢን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ።

8“ ‘አንዱን ወይፈን ለተለየ ስለት ወይም ለኅብረት የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት
በተለምዶ የድነት መሥዋዕት ይባላል።
ወይም የዕርድ መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በምታዘጋጁበት ጊዜ፣
9ከወይፈኑ ጋር በግማሽ ኢን
ስድስት ተኩል ሊትር ያህል ነው።
ዘይት የተለወሰ የኢፍ
ሁለት ሊትር ያህል ነው።
ሦስት ዐሥረኛ የላመ ዱቄት አብራችሁ አምጡ።
10እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን ግማሽ ኢን የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብና ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል። 11እያንዳንዱ ወይፈን ወይም አውራ በግ፣ እያንዳንዱ የበግም ሆነ የፍየል ጠቦት በዚህ ሁኔታ ይዘጋጅ። 12ባዘጋጃችሁት ቍጥር ልክ ይህን ለእያንዳንዱ አድርጉ።

13“ ‘ማናቸውም የአገር ተወላጅ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ያድርግ። 14ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ መጻተኛ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማናቸውም ሰው በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ። 15ማኅበረ ሰቡ ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ አንድ ዐይነት ደንብ ይኖረዋል፤ ይህም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ የማይሻር ሥርዐት ነው። እናንተም ሆናችሁ መጻተኞቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እኩል ትታያላችሁ፤ 16ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ ይኸው ሕግና ሥርዐት እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።’ ”

17 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 18“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘እኔ ወደምወስዳችሁ ምድር ገብታችሁ፣ 19የምድሪቱን በረከት ስትመገቡ ከዚሁ ላይ አንሥታችሁ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍርባን አቅርቡ። 20ይህንም ከመጀመሪያው ዱቄት ላይ ኅብስት ጋግራችሁ ከዐውድማ እንደ ተገኘ ቍርባን አድርጋችሁ አምጡ። 21በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ዱቄት ላይ አንሥታችሁ ይህን ቍርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ትሰጣላችሁ።

ባለማወቅ ስለሚደረግ ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት

22“ ‘እንግዲህ ካለማወቅ የተነሣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ ከሰጣቸው ትእዛዞች አንዱን ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ይህም ማለት 23እግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዞቹን ከሰጠበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ ትውልዶች በሙሴ አማካይነት ያዘዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ባታደርጉ፣ 24ይህም የተፈጸመው ሆን ተብሎ ሳይሆንና ማኅበረ ሰቡም ሳያውቀው ከሆነ፣ ማኅበረ ሰቡ በሙሉ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ አድርጎ አንድ ወይፈን በእሳት ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚሁም ጋር ሥርዐቱ የሚጠይቀውን የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ደግሞም ለኀጢአት መሥዋዕት ተባዕት ፍየል ያቅርብ። 25ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ያስተሰርያል፤ እነርሱም ይቅር ይባላሉ፤ ምክንያቱም ባለማወቅ የተፈጸመ ስለ ሆነና ስለ ስሕተታቸውም በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኀጢአት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) ስላቀረቡ ነው። 26ባለማወቅ የተደረገውን ስሕተት ሁሉም የፈጸሙት ስለሆነ፣ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብና በመካከላቸው የሚኖር መጻተኛ ሁሉ ይቅር ይባላል።

27“ ‘ነገር ግን አንድ ሰው ካለማወቅ የተነሣ በግሉ ኀጢአት ቢሠራ ግን ለኀጢአት መሥዋዕት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያምጣ። 28ከዚያም ካህኑ፣ ባለማወቅ ኀጢአት ሠርቶ ለተሳሳተው ሰው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይለታል፤ ስርየት በሚደረግለትም ጊዜ ሰውየው ይቅር ይባላል። 29ያገር ተወላጅ እስራኤላዊ ይሁን ወይም መጻተኛ ባለማወቅ ኀጢአት ከሠራ በማናቸውም ሰው ላይ ሕጉ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

30“ ‘ያገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ ሆን ብሎ ኀጢአት የሚሠራ ማንኛውም ሰው ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ስለሚያቃልል ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ። 31የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃል ስለናቀ፣ ትእዛዞቹንም ስለ ጣሰ ያ ሰው በርግጥ ተለይቶ መጥፋት አለበት፤ ጥፋቱ የራሱ ነው።’ ”

ሰንበትን የሻረው በሞት ተቀጣ

32እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ አንድ ሰው በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም ተገኘ። 33ዕንጨት ሲለቅም ያገኙትም ሰዎች ሰውየውን ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበር አመጡት፤ 34በሰውየው ላይ ምን መደረግ እንዳለበት ግልጽ የሆነ ነገር ባለመኖሩ በጥበቃ ሥር እንዲቈይ አደረጉት። 35ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “ሰውየው ይሙት፤ መላውም ማኅበር ከሰፈር ውጭ በድንጋይ ይውገረው” አለው፤ 36ስለዚህ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ማኅበሩ ሰውየውን ከሰፈር አውጥቶ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወገረው።

ስለ ልብስ ዘርፍ የተሰጠ መመሪያ

37 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 38“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ በየልብሳችሁ ጫፍ ላይ ዘርፍ አድርጉ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ሰማያዊ ጥለት ይኑረው። 39ልባችሁ የተመኘውን፣ ዐይናችሁ ያየውን ሁሉ ተከትላችሁ እንዳታመነዝሩ እነዚህን ዘርፎች በማየት የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ትእዛዞች በማስታወስ እንድትታዘዙ ማስታወሻ ይሆኗችኋል። 40ስለዚህ ትእዛዞቼን ሁሉ ለመፈጸም ታስባላችሁ፤ ለአምላካችሁም (ኤሎሂም) የተቀደሳችሁ ትሆናላችሁ። 41አምላካችሁ (ኤሎሂም) እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ነኝ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።’ ”

Copyright information for AmhNASV