1 Chronicles 25

የቤተ መቅደሱ መዘምራን

1ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገናና በጸናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶታም ቤተ ሰብ መካከል መርጦ መደበ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፤

2ከአሳፍ ወንዶች ልጆች፤
ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። የአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሡ አመራር ሥር ነበረ።
3ከኤዶታም ወንዶች ልጆች፤
ጎዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ
አንድ የዕብራይስጥ ቅጅና ጥቂት የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም ቍጥር 17 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ስሜኢ የሚለውን አይጨምሩም
፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
4ከኤማን ወንዶች ልጆች፤
ቡቅያ፣ መታንያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ሐናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።
5እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለ ራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ሰጡት
ዕብራይስጡ፣ ቀንዱ ከፍ ከፍ አለ ይላል
። እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።

6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጸናጽል፣ በመሰንቆና በበገና ድምፅ ለሚቀርበው የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሡ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ። 7እነዚህም ከቤተ ዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑና የተካኑ ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
8
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።

 9የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ለዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ
የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ የሚለውን አይጨምርም
ቍጥራቸውም 12
ድምሩን በተመለከተ ቍጥር 7 ይመ፤ ዕብራይስጡ፣ “12” የሚለውን አይጨምርም
ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤
ቍጥራቸውም 12
 10ሦስተኛው ለዛኩር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 11አራተኛው ለይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 12አምስተኛው ለነታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 13ስድስተኛው ለቡቅያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 14ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቁጥራቸውም 12
 15ስምንተኛው ለየሻያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቁጥራቸውም 12
 16ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቁጥራቸውም 12
 17ዐሥረኛው ለሰሜኢ ወጣ፤ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 19ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 21ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 22ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 24ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 25ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 26ዐሥራ ዘጠነኛው ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 27ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 28ሃያ አንደኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 29ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 30ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12
 31ሃያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤
ቍጥራቸውም 12።

31
Copyright information for AmhNASV