2 Samuel 23:8
የኀያላኑ የዳዊት ሰዎች ጀብዱ
23፥8-39 ተጓ ምብ – 1ዜና 11፥10-41 8የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤
የታሕክሞን ▼▼የታሕክሞን ሰው ማለት
ሐክሞናዊ ማለት ሊሆን ይችላል። (
1ዜና 11፥11 ይመ)።
ሰው ዮሴብ በሴትቤት ▼▼ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ግን፣
ኢያሱስቴ ይላሉ፣ ይኸውም፣
ያሾብዓም ነው (
1ዜና 11፥11 ይመ)።
የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው። ▼▼አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ (
1ዜና 11፥11 ይመ)፤ ዕብራይስጡና አብዛኞቹ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ግን
ስምንት መቶ ሰዎችን የገደለው አዜናዊው አዲኑ ነበር ይላሉ።