Amos 9

እስራኤል ትጠፋለች

1ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤

“መድረኮቹ እንዲናወጡ፣
ጕልላቶቹን ምታ፤
በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤
የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤
ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤
ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።
2መቃብር
ዕብራይስጡ ሲዖል ይለዋል።
በጥልቀት ቈፍረው ቢወርዱም፣
እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤
ወደ ሰማይ ቢወጡም፣
ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።
3በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣
ዐድኜ፣ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤
እይዛቸዋለሁም።
በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣
በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዝዘዋለሁ፤
4በጠላቶቻቸው ተነድተው ለምርኮ ቢወሰዱም፣
በዚያ እንዲገድላቸው ሰይፍን አዝዛለሁ፤

“ለመልካም ሳይሆን ለክፉ፣
ዐይኔን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ።”

5ጌታ፣ እግዚአብሔር ጸባኦት፣
ምድርን ይዳስሳል፤
እርሷም ትቀልጣለች፤
በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤
የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤
እንደ ግብፅ ወንዝም ይወርዳል።
6መኖሪያውን
ዕብራይስጡ ለዚህ ሐረግ የሰጠው ትርጕም ምን እንደ ሆነ አይታወቅም።
በሰማይ የሚሠራ፣
መሠረቱንም
ዕብራይስጡ ለዚህ ሐረግ የሰጠው ትርጕም ምን እንደ ሆነ አይታወቅም።
በምድር የሚያደርግ፣
የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣
በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስስ፣
እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።

7“እናንት እስራኤላውያን፣
ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?”
ይላል እግዚአብሔር
“እስራኤልን ከግብፅ፣
ፍልስጥኤማውያንን ከከፍቶር
በላይኛው አባይ አካባቢ ያለ ሕዝብ ነው።

ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

8“እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣
በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤
ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤
የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉ
አልደመስስም፤”
ይላል እግዚአብሔር
9“እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤
እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣
የእስራኤልን ቤት፣
በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤
ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
10በሕዝቤ መካከል ያሉ፣
‘ክፉ ነገር አያገኘንም ወይም አይደርስብንም’ የሚሉ፣
ኀጢአተኞች ሁሉ፣
በሰይፍ ይሞታሉ።

የእስራኤል መመለስ

11“በዚያ ቀን፣

“የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፤
የተሰበረውን እጠግናለሁ፤
የፈረሰውን ዐድሳለሁ፤
ቀድሞ እንደ ነበረም አድርጌ እሠራዋለሁ፤
12ስለዚህ የኤዶምን ትሩፍ፣
በስሜ
ዕብራይስጡ እንደ ሰብዓ ሊቃናቱ ትርጕም የሕዝቡ ትሩፋንና ስሜን የሚሸከሙ ሁሉ፣ እኔን ይፈልጋሉ
የተጠሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ይወርሳሉ፤”
ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር
13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ ዐጫጁ ዐጭዶ ሳይጨርስ፣
ዐራሹ በላዩ የሚደርስበት፣
ችግኝ ተካዩም ገና ተክሎ ሳይጨርስ፣
ወይን ጨማቂው የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፤
አዲስ የወይን ጠጅ ከተራሮች ይንጠባጠባል፤
ከኰረብቶችም ሁሉ ይፈስሳል።
14የተሰደደውን
ወይም ዕጣ ፈንታቸውን አድሳለሁ
ሕዝቤን እስራኤልን እመልሳለሁ።

“እነርሱም የፈራረሱትን ከተሞች መልሰው ሠርተው በውስጣቸው ይኖራሉ።
የወይን ተክል ተክለው፣ ጠጁን ይጠጣሉ፤
አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።
15እስራኤልን በገዛ ምድራቸው እተክላቸዋለሁ፤
ከሰጠኋቸውም ምድር፣
ዳግመኛ አይነቀሉም፤”
ይላል አምላክህ እግዚአብሔር

Copyright information for AmhNASV