Ezekiel 40

አዲሱ ቤተ መቅደስ

1በተሰደድን በሃያ አምስተኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በዐሥረኛው ቀን፣ ከተማዪቱ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበር፤ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ። 2በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ ከተራራውም በስተ ደቡብ፣ ከተማ የሚመስሉ ሕንጻዎች ነበሩ። 3ወደዚያ ወሰደኝ፤ እነሆ መልኩ ናስ የሚመስል ሰው አየሁ፤ እርሱም የሐር ገመድና መለኪያ ዘንግ በእጁ ይዞ በመግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር። 4ሰውየውም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐይንህ እይ፤ በጆሮህ ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፤ ወደዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና ያየኸውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”

ወደ ውጩ አደባባይ የሚያወጣው የምሥራቅ በር

5የቤተ መቅደሱን ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የከበበ ቅጥር አየሁ፤ በሰውየውም እጅ ርዝመቱ ስድስት ክንድ የሆነ መለኪያ ዘንግ አየሁ፤ እያንዳንዱ ክንድ፣ አንድ ክንድ ከስንዝር ነበር፤ እርሱም ቅጥሩን ለካው፤ ስፋቱ አንድ መለኪያ ዘንግ ሲሆን፣ ቁመቱም እንዲሁ አንድ መለኪያ ዘንግ ነበር።

6ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር መጣ፤ ደረጃዎቹን ወጥቶ የበሩን መግቢያ መድረክ ለካ፤ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።
ከሰብዓ ሊቃናት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን የመጀመሪያው ጕበን ርዝመቱ አንድ ዘንግ ነበር ይላል።
7የዘብ ጠባቂ ቤቶች፣ ቁመታቸው አንድ መለኪያ ዘንግ፣ ወርዳቸውም አንድ መለኪያ ዘንግ ነበር፤ በቤቶቹም መካከል ያሉት ግንቦች ውፍረት አምስት ክንድ ነበር። ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ባለው መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ መድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበር።

8ከዚያም የመግቢያውን በር መተላለፊያውን በረንዳ ለካ፤ 9ቁመቱ
በብዙ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች በሰብዓ ሊቃናት፣ በቩልጌትና በሱርስቱም እንዲሁ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች ግን በቤተ መቅደሱ ትይዩ ያለ፣ የመግቢያ በር ነው፤ አንድ ክንድ ነበር 9 ከዚያም የመግቢያ በሩን መተላለፊያ በረንዳ ለካው ይላሉ።
ስምንት ክንድ፣ የዐምዶቹም ውፍረት ሁለት ክንድ ነበር። የመግቢያው በር መተላለፊያ በረንዳ፣ ከቤተ መቅደሱ ትይዩ ነው።

10በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ መጠናቸው እኩል የሆነ ሦስት ሦስት የዘብ ቤቶች ነበሩ፤ በመካከላቸው ወጣ ወጣ ብለው የሚታዩትም ግንቦች ተመሳሳይና እኩል ነበሩ። 11ከዚያም የበሩን ስፋት ለካ፤ ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱም ዐሥራ ሦስት ክንድ ነበር። 12በእያንዳንዱ ዘብ ቤት ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ የግንብ ዐጥር አለ፤ የዘብ ቤቶቹም ስፋት እኩል በኩል ስድስት ክንድ ነበር። 13ከዚያም ከዘብ ቤቱ የኋላ ግድግዳ ጀምሮ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ያለውን የመግቢያ በር ለካ፤ ከአንዱ መከለያ ግድግዳ እስከ ሌላው መከለያ ግድግዳ ያለው ርቀት ሃያ አምስት ክንድ ነበር። 14በመግቢያው በር ዙሪያ ባሉት ወጣ ወጣ ባሉት ግንቦች ሁሉ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ ለካ፤ ስድሳ ክንድም ነበር። የተለካውም ከአደባባዩ
ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን ወጣ ያለ ግንብ ይለዋል።
ፊት ለፊት እስካለው መተላለፊያ በረንዳ
በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም።
ድረስ ነበር።
15ከበሩ መግቢያ እስከ መተላለፊያ በረንዳው መጨረሻ ድረስ ያለው ርቀት አምሳ ክንድ ነበር። 16ክፍሎቹ እንደ መተላለፊያ በረንዳዎቹ ከግራና ከቀኝ በኩል ትንንሽ መስኮቶች አሏቸው። በዙሪያው ያሉ መስኮቶች በመግቢያው በር ፊት ለፊት የነበሩ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ክፍል ግራና ቀኝ ግድግዳ ላይ ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾበታል።

የውጩ አደባባይ

17ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ እዚያም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ክፍሎችና ድንጋይ የተነጠፈበት መመላለሻ አየሁ፤ በመመላለሻውም ዙሪያ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ። 18የታችኛው ንጣፍ ወለል ከመግቢያው በር ጋር ተያይዞ የተሠራ ሲሆን፣ ስፋቱ እንደ በሮቹ ርዝመት መጠን ነበር። 19ከዚያም ከታችኛው መግቢያ በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ያለውን ርቀት ለካ፤ በምሥራቅም ሆነ በሰሜን በኩል ያለው ርቀት አንድ መቶ ክንድ ነበር።

የሰሜኑ በር

20ከዚያም በሰሜን ትይዩ ያለውን፣ ወደ ውጩ አደባባይ የሚያመራውን በር ርዝመትና ወርድ ለካ። 21እንደ መጀመሪያው በር ሁሉ ይኸኛውም በየጐኑ ያሉት ሦስት ሦስት የዘብ ቤቶች፣ በየመካከሉ ወጣ ወጣ ያሉ ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው እኩል ነበር። ርዝመቱ አምሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበር። 22መስኮቶቹ፣ መተላለፊያ በረንዳዎቹና የዘንባባ ዛፍ ቅርጾቹ ልካቸው በምሥራቁ በር ካሉት ጋር ተመሳሳይ ነበር። ወደዚያ የሚያመሩ ሰባት ደረጃዎች አሉ፤ መተላለፊያ በረንዳዎቹም ከእነርሱ ጋር ትይዩ ነበር። 23ልክ በምሥራቅ በኩል እንዳለው ሁሉ፣ ከሰሜኑ በር ጋር ትይዩ የሆነ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያመራ በር አለ። ከአንዱ በር እስከ ሌላኛው በር ያለውን ለካው፤ ይህም አንድ መቶ ክንድ ነበር።

የደቡቡ በር

24ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ መራኝ፤ እዚያም ፊቱን ወደ ደቡብ ያደረገ በር አየሁ፤ እርሱም የውስጠኛውን ግድግዳና መተላለፊያ በረንዳውን ለካ፤ የእነዚህም መጠን እንደ ሌሎቹ በሮች ነበር። 25የመግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳው እንደ ሌሎቹ ሁሉ በዙሪያው ጠባብ መስኮቶች ነበሩት፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ፤ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበር። 26ከመተላለፊያ በረንዳው ትይዩ የሆኑ ሰባት ደረጃዎች ወደ መግቢያው በር ያመራሉ፤ ወጣ ወጣ ብለው በሚታዩ ግድግዳዎችም ላይ የዘንባባ ቅርጽ አለ። 27ውስጠኛው አደባባይ ደግሞ ከደቡብ ጋር ትይዩ የሆነ በር አለው፤ እርሱም ከዚህ በር አንሥቶ በደቡብ አቅጣጫ እስካለው እስከ ውጭው በር ድረስ ለካው፤ ይህም አንድ መቶ ክንድ ሆነ።

ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገቡ በሮች

28ከዚያም በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ የደቡብንም በር ለካው፤ መጠኑም እንደ ሌሎቹ በሮች ነበር። 29የዘብ ቤቶቹ፣ በየመካከሉ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር። መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳዎቹ በዙሪያቸው መስኮቶች ነበሯቸው። ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበር። 30በውስጠኛው አደባባይ ዙሪያ ያሉት የመግቢያው በር መተላለፊያ በረንዳዎቹ ርዝመት ሃያ አምስት ክንድ ሲሆን፣ ወርዳቸው ደግሞ አምስት ክንድ ነበር። 31መተላለፊያ በረንዳው ከውጭው አደባባይ ጋር ትይዩ ነው፤ የዘንባባ ዛፎች በዐምዶቹ ላይ ተቀርጸዋል፤ እስከ መግቢያው ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

32ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ መግቢያ በሩንም ለካው፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር። 33የዘብ ቤቶቹ፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር፤ መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳው ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩት፤ የዚህም ርዝመቱ አምሳ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ አምስት ክንድ ነበር። 34መተላለፊያ በረንዳው ከውጩ አደባባይ ትይዩ ነው፤ በዐምዶቹ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጿል፤ እስከ መግቢያ ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

35ከዚያም ወደ ሰሜን በር አመጣኝ፤ ለካውም፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር። 36የዘብ ቤቶቹ፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦቹና መተላለፊያ በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር፤ በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩት። የዚህም ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበር። 37መተላለፊያ በረንዳው
ሰብዓ ሊቃናቱም (በተጨማሪ 31 እና 34 ይመ) እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን መቃኖች ይላል።
ከውጩ አደባባይ ትይዩ ነው፤ በዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጿል፤ እስከ መግቢያው ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

መሥዋዕት የሚዘጋጅባቸው ክፍሎች

38በእያንዳንዱ የውስጥ መግቢያ በር መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚታጠብበት በር ያለው ክፍል አለ። 39በመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳው ሥር በግራና በቀኝ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የኀጢአትና የበደል መሥዋዕት የሚታረዱበት ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች አሉ። 40ከመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳ በስተ ውጭው ግንብ ወደ ሰሜን በር መግቢያ ላይ ባሉት ደረጃዎች አጠገብ ከግራና ከቀኝ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ይገኛሉ። 41ስለዚህ በአንዱ በር በኩል አራት፣ በሌላውም በኩል አራት ጠረጴዛዎች፤ መሥዋዕቱ የሚታረድባቸው በድምሩ ስምንት ጠረጴዛዎች አሉ ማለት ነው። 42ለሚቃጠለው መሥዋዕት መገልገያ የሆኑ፣ ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ የእያንዳንዳቸው ርዝመት፣ ወርድና ቁመት አንድ ክንድ ተኩል ነበር፤ በእነዚህም ላይ ለሚቃጠለው መሥዋዕትና ለሌላውም መሥዋዕት ማረጃ የሚሆኑ መሣሪያዎች ይቀመጡባቸው ነበር። 43እንዲሁም አንዳንድ ስንዝር የሚሆኑ ሁለት ጣት ያላቸው ሜንጦዎች በግንቡ ዙሪያ ተንጠልጥለው ነበር፤ ጠረጴዛዎቹም የመሥዋዕቱ ሥጋ ማስቀመጫ ነበሩ።

ለካህናት የተመደቡ ክፍሎች

44በውስጠኛው አደባባይ፣ ከውስጠኛው በር ውጭ፣ ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ አንዱ
ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን የመዘመራን ክፍሎች ነበሩ ይላል።
በደቡብ
ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን በምሥራቅ ይላል።
ትይዩ በሰሜን በር በኩል ሲሆን፣ ሌላው በሰሜን ትይዩ በደቡብ በር በኩል ነበር።
45እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “በደቡብ ትይዩ ያለው ክፍል በቤተ መቅደስ ውስጥ ለሚያገለግሉ ካህናት ሲሆን፣ 46በሰሜን ትይዩ ያለው ክፍል ደግሞ በመሠዊያው ላይ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህም የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ማገልገል የሚችሉ ሌዋውያን እነርሱ ብቻ ናቸው።”

47ከዚያም አደባባዩን ለካው፤ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ መቶ ክንድ እኩል በእኩል ባለ አራት ማእዘን ነበር። መሠዊያውም በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ነበር።

ቤተ መቅደሱ

48ወደ ቤተ መቅደሱም መተላለፊያ በረንዳ አመጣኝ፤ የመተላለፊያ በረንዳዎቹን ዐምዶች ለካ፤ በአንዱ በኩል አምስት ክንድ በሌላውም እንዲሁ አምስት ክንድ ነበር። የመግቢያው በር ርዝመት ዐሥራ አራት ክንድ ሲሆን፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ስፋት በአንዱ በኩል ሦስት ክንድ፣ በሌላውም እንዲሁ ሦስት ክንድ ነበሩ።
ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች መግቢያ… ነበሩ ይላል።
49የመተላለፊያው በረንዳ ርዝመት ሃያ ክንድ፣ ከፊት እስከ ኋላ ያለውም ወርድ ዐሥራ ሁለት
ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን ዐሥራ አንድ ይላል።
ክንድ ነበር። ወደ ቤተ መቅደሱም የሚያደርሱ ዐሥር ደረጃዎች የነበሩ ሲሆን፣ በየዐምዱም ጐንና ጐን ምሰሶዎች ነበሩ።

Copyright information for AmhNASV