Isaiah 53

1የሰማነውን ነገር ማን አመነ?
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?
2በፊቱ እንደ ቡቃያ፣
ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤
የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤
እንድንወድደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።
3በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣
የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር።
ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣
የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።

4በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤
ሕመማችንንም ተሸከመ፤
እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣
እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው።
5ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤
ስለ በደላችንም ደቀቀ፤
በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤
በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
6እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤
እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤
እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል
በእርሱ ላይ ጫነው።

7ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤
ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤
እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤
በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣
አፉን አልከፈተም።
8በማስጨነቅና
ወይም፣ በእስር
በፍርድ ተወሰደ፤
ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመትቶ፣
ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣
ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
9በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣
ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣
አሟሟቱ ከክፉዎች፣
መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ።

10መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤
እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣
ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤
የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
11ከነፍሱ ሥቃይ በኋላ፣
የሕይወት ብርሃን
የሙት ባሕር ጥቅሎች (እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምን ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ የሕይወት ብርሃን የሚለውን ሐረግ አይጨምርም።
ያያል፤ ደስም ይለዋል፤
ጻድቅ ባሪያዬ በዕውቀቱ ብዙዎቹን ያጸድቃል፤
መተላለፋቸውንም ይሸከማል።
12ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች
ወይም፣ ከብዙዎች ጋር
ጋር እሰጠዋለሁ፤
ምርኮውን ከኀያላን
ወይም፣ እጅግ ብዙ ከሆኑ ጋር
ጋር ይካፈላል፤
እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣
ከክፉ አድራጊዎችም ጋር በመቈጠሩ፣
የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤
ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።
Copyright information for AmhNASV