Nehemiah 7

1ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ። 2በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው። 3ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያደርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።

ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር

4ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር። 5ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።

6የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ።
7
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የተመለሱትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋር ነው።

የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፦
 8ከፋሮስ ዘሮች 2,172
 9ከሰፋጥያስ ዘሮች 372
 10ከኤራ ዘሮች 652
 11ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,818
 12ከኤላም ዘሮች 1,254
 13ከዛቱዕ ዘሮች 845
 14ከዘካይ ዘሮች 760
 15ከቢንዊ ዘሮች 648
 16ከቤባይ ዘሮች 628
 17ከዓዝጋድ ዘሮች 2,322
 18ከአዶኒቃም ዘሮች 667
 19ከበጉዋይ ዘሮች 2,067
 20ከዓዲን ዘሮች 655
 21በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ ከአጤር ዘሮች 98
 22ከሐሱም ዘሮች 328
 23ከቤሳይ ዘሮች 324
 24ከሐሪፍ ዘሮች 112
 25ከገባዖን ዘሮች 95
 26ከቤተ ልሔምና ከነጦፋ ሰዎች 188
 27ከዓናቶት ሰዎች 128
 28ከቤት አዝሞት ሰዎች 42
 29ከቂርያትይዓሪም፣ ከከፊራና ከብኤሮት ሰዎች 743
 30ከራማና ከጌባ ሰዎች 621
 31ከማክማስ ሰዎች 122
 32ከቤቴልና ከጋይ ሰዎች 123
 33ከሌላው ናባው ሰዎች 52
 34ከሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
 35ከካሪም ዘሮች 320
 36ከኢያሪኮ ዘሮች 345
 37ከሎድ፣ ከሐዲድና ከኦኖም ዘሮች 721
 38ከሴናዓ ዘሮች 3,930


39
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
ካህናቱ፦
በኢያሱ ቤተ ሰብ መሥመር ከዮዳኤ ዘሮች 973
 40ከኢሜር ዘሮች 1,052
 41ከፋስኮር ዘሮች 1,247
 42ከካሪም ዘሮች 1,017


43ሌዋውያኑ፦


በቀድምኤል በኩል በሆዳይዋ የትውልድ መሥመር የኢያሱ ዘሮች     74


44መዘምራኑ፦


ከአሳፍ ዘሮች     148


45በር ጠባቂዎቹ፦


ከሰሎም፣ ከአጤር፣ ከጤልሞን፣ ከዓቁብ፣ ከሐጢጣና ከሶባይ ዘሮች     138


46
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
ከሲሐ፣ ከሐሡፋ፣ ከጠብዖት ዘሮች፣
 47ከኬራስ፣ ከሲዓ፣ ከፋዶን፣
 48ከልባና፣ ከአጋባ፣ ከሰምላይ ዘሮች፣
 49ከሐናን፣ ከጌዴል፣ ከጋሐር ዘሮች፣
 50ከራያ፣ ከረአሶን፣ ከኔቆዳ ዘሮች፣
 51ከጋሴም፣ ከዖዛ፣ ከፋሴሐ ዘሮች፣
 52ከቤሳይ፣ ከምዑኒም፣ ከንፉሰሲም ዘሮች፣
 53ከበቅቡቅ፣ ከሐቀፋ፣ ከሐርሑር ዘሮች፣
 54ከበስሎት፣ ከምሒዳ፣ ከሐርሻ ዘሮች፣
 55ከቦርቆስ፣ ከሲሣራ፣ ከቴማ ዘሮች፣
 56ከንስያ፣ ከሐጢፋ ዘሮች።

57
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
የሶጣይ፣ የሶፌሬትና፣ የፍሩዳ ዘሮች፣
 58የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጊዴል ዘሮች፣
 59የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈከራት ዘሮች፣ የሐፂቦይምና የአሞን ዘሮች።
 60የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አሽከሮች ዘሮች 392


61
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የተመለሱ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
 62የዳላያ፣ የጦብያ፣ የኔቆዳ ዘሮች 642


63ከካህናቱ መካከል፦
የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።
64እነዚህ የየቤተ ሰቡ ትውልድ ሐረጋቸውን ከመዝገብ ለማግኘት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ። 65ስለዚህም አገረ ገዥው በኡሪምና በቱሚም አገልግሎት የሚሰጥ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።

66የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤ 67ይህ 7,337 የወንድና የሴት አገልጋዮቻቸውን አይጨምርም፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። 68736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች
አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች (እንዲሁም ዕዝ 2፥66) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ይህን ጥቅስ አይጨምሩም።
69435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።

70አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ
8.5 ኪሎ ግራም ያህል ነው።
፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።
71ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ
170 ኪሎ ግራም ያህል ነው።
2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
72የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ
1.1 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው።
2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።

73ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።

ዕዝራ ሕጉን አነበበ

ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣

Copyright information for AmhNASV