Numbers 5

የሰፈሩ መንጻት

1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ተላላፊ የቈዳ በሽታ
በተለምዶ ለምጽ ማለት ነው፤ የዕብራይስጡ ትርጕም ለምጽን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የቈዳ በሽታዎችን የሚያመለክት ነው።
ያለበትን ወይም ማንኛውም ዐይነት ፈሳሽ ከሰውነቱ የሚወጣውን ወይም ሬሳ በመንካቱ በሥርዐቱ መሠረት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እስራኤላውያንን እዘዝ፤
3ወንድም ሆነ ሴት አስወጡ፤ እኔ በመካከላቸው የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈር አስወጧቸው።” 4እስራኤላውያን ይህንኑ አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈር አስወጧቸው፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ፈጸሙ።

የካሳ አከፋፈል

5 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 6“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ወንድም ሆነ ሴት በማናቸውም ረገድ ሌላውን ቢበድልና ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ያለውን ታማኝነት ቢያጐድል ያ ሰው በደለኛ ነው 7በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ስለ በደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ አምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤ 8ነገር ግን ይህ ሰው ካሳውን የሚቀበልለት ዘመድ ከሌለው ካሳው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ስለሚሆን ማስተስረያ እንዲሆነው ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋር ለካህኑ ይስጥ። 9እስራኤላውያን የሚያመጧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ሁሉ ለተቀባዩ ካህን ይሆናሉ፤ 10የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሰ ስጦታ ለካህኑ ይሆናል፤ ለካህኑ የሚሰጠውም ሁሉ የራሱ ይሆናል።’ ”

በአመንዝራነት ስለሚጠረጠሩ ሚስቶች

11ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 12“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘አንዲት ባለ ትዳር ሴት ወደ ሌላ ወንድ በማዘንበል ለባሏ ያላትን ታማኝነት አጕድላ፣ 13ከሌላ ሰው ጋር ብትተኛ፣ ይህም እጅ ከፍንጅ ባለመያዟ ምክንያት ይህ ከባሏ ቢደበቅ፣ የሚመሰክርባት ሰው ባይኖርና መርከሷም ባይገለጥ፣ 14ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና በርግጥም ጐድፋ ብትገኝ ወይም ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና እርሷ ግን ጐድፋ ባትገኝ፣ 15ወደ ካህኑ ይውሰዳት፤ ስለ እርሷም አንድ ኪሎ
የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ማለት ነው።
ገብስ ዱቄት ለቍርባን ይውሰድ፤ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ ይህ ስለ ቅናት የቀረበ የእህል ቍርባን በደልን የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና።

16“ ‘ካህኑ ሴትየዋን ያመጣትና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንድትቆም ያደርጋታል፤ 17ከዚያም የተቀደሰ ውሃ በሸክላ ዕቃ ቀድቶ በማደሪያው ድንኳን ካለው ወለል ጥቂት ዐፈር ቈንጥሮ በውሃው ውስጥ ይጨምራል። 18ካህኑ ሴትየዋን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንድትቆም ካደረገ በኋላ የጠጕሯን መሸፈኛ ይገልጣል፤ ስለ ቅናት የቀረበውን የመታሰቢያ ቍርባን በእጇ ያስይዛታል፤ ከዚያም ካህኑ ርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ በእጁ ይይዛል። 19ካህኑም ሴትየዋን ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፤ “ሌላ ወንድ አብሮሽ ካልተኛ፣ በትዳር ላይ ሆነሽ ወደ ርኩሰት ካላዘነበልሽ ይህ ርግማን የሚያመጣ መራራ ውሃ ጕዳት አያድርስብሽ፤ 20ነገር ግን በትዳር ላይ እያለሽ ወደ ርኩሰት በማዘንበል ከባልሽ ሌላ ከወንድ ጋር በመተኛት ከጐደፍሽ”፣ 21እዚህ ላይ ካህኑ እንዲህ በማለት ሴትየዋን በርግማን መሐላ ያስምላታል፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ጭንሽን እያሰለለና
ሴቶች ያስወርዱ ወይም መካን ይሁኑ ማለት ነው።
ሆድሽን እያሳበጠ በሕዝብሽ መካከል ርግማንና መሐላ ያድርግብሽ፤
22ይህን ርግማን የሚያመጣ ውሃ በጠጣሽ ጊዜም ሆድሽን ያሳብጠው፤ ጭንሽን ያስልለው።”

“ ‘ሴትዮዋም፣ “አሜን፤ አሜን” ትበል።

23“ ‘ካህኑ እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጻፍ፤ በመራራውም ውሃ ይደምስሳቸው። 24ርግማን የሚያመጣውንም ውሃ ሴትየዋ እንድትጠጣ ያድርግ፤ ውሃውም ወደ ሰውነቷ ገብቶ የመረረ ሥቃይ ያስከትልባታል። 25ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቍርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው። 26ካህኑ የመታሰቢያ ቍርባን እንዲሆን ዕፍኝ የእህል ቍርባን ከዚያ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ከዚያም በኋላ ሴቲቱ ውሃውን እንድትጠጣ ያድርግ። 27ራሷን በማጕደፍ ለባሏ ያላትን ታማኝነት አጕድላ ከሆነ፣ ርግማን የሚያመጣውን ውሃ እንድትጠጣ ሲደረግ ውሃው ወደ ሰውነቷ ገብቶ ክፉ ሥቃይ ያመጣባታል፤ ሆዷ ያብጣል
ትመክናለች ወይም ታስወርዳለች ማለት ነው።
፤ ጭኗ ይሰልላል፤ በሕዝቦቿም ዘንድ የተረገመች ትሆናለች።
28ዳሩ ግን ሴትየዋ ካልጐደፈችና ነውር ከሌለባት ከበደሉ ነጻ ትሆናለች፤ ልጆችም ትወልዳለች።

29“ ‘እንግዲህ የቅናት ሕግ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በትዳር ላይ እያለች ወደ ሌላ ሄዳ ከረከሰች፣ 30ወይም አንድ ሰው ሚስቱን ከመጠርጠሩ የተነሣ የቅናት መንፈስ ሲያድርበት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቁማት፤ ካህኑም ሕጉ በሙሉ በሴቲቱ ላይ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ያድርግ። 31ባልየውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፤ ሴትየዋ ግን በበደሏ ምክንያት የሚመጣውን ፍዳ ትቀበላለች።’ ”

Copyright information for AmhNASV