Psalms 11

የጻድቃን ትምክሕት

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።

1 በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤
ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ”
ለምን ትሏታላችሁ?
2ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?
“ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤
የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣
ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።
3መሠረቱ ከተናደ፣
ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?”
ወይም ጻድቁ ምን እያደረገ ነው?


4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤
የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።
ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤
ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5 እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጥኡን ይመረምራል፤
ወይም ጻድቁ እግዚአብሔር ኀጥኡን ይመረምራል

ዐመፃን የሚወድዱትን ግን፣
ነፍሱ ትጠላቸዋለች።
6እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤
የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣
የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።

7 እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤
የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤
ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።
Copyright information for AmhNASV