Psalms 123

የተጨነቀ ሰው ጸሎት

መዝሙረ መዓርግ።

1በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጥህ ሆይ፤
ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣለሁ።
2የባሪያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ፣
የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት፣
ምሕረት እስከሚያደርግልን ድረስ፣
የእኛም ዐይኖች ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ።

3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንቀት በዝቶብናልና፣
ማረን፤ እባክህ ማረን።
4ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣
የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል።
Copyright information for AmhNASV