Psalms 14

አምላክ የለሽ ሰዎች

14፥1-7 ተጓ ምብ – መዝ 53፥1-6

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።

1ሞኝ
በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ሞኝ ወይም ተላላ ተብለው የተተረጐሙት የዕብራይስጥ ቃላት ግብረ ገባዊ ንቅዘትን የሚያመለክቱ ናቸው።
በልቡ፣
“እግዚአብሔር የለም” ይላል።
ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤
በጎ ነገር የሚሠራ አንድም የለም።

2የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ መኖሩን ለማየት፣
እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤
በአንድ ላይም ብልሹ ሆነዋል፤
አንድ እንኳ፣
መልካም የሚያደርግ የለም።

4 የእግዚአብሔርን ስም የማይጠሩት፣
ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣
ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ዕውቀት የላቸውምን?
5ባሉበት ድንጋጤ ውጧቸዋል፤
እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።
6እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤
እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።

7ምነው እስራኤልን የሚያድን ከጽዮን በወጣ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣
ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።
Copyright information for AmhNASV