Psalms 145

ምስጋና ለንጉሡ ለእግዚአብሔር

የዳዊት የምስጋና መዝሙር።

1አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤
ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።
2በየቀኑ እባርክሃለሁ፤
ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

3 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤
ታላቅነቱም አይመረመርም።
4ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤
ብርቱ ሥራህን ያውጃል።
5ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤
ስለ ድንቅ ሥራህም
የሙት ባሕር ጥቅልሎች እና ሱርስት (የሰብዓ ሊቃናትን ትርጕም ይመ) ስለ ግርማህ ታላቅነትና ክብር፣ ዕፁብ ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ ይላሉ።
ያወራሉ።
6ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤
እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።
7የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤
ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።

8 እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው፤
ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱ የበዛ።

9 እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤
ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።
10 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤
ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።
11ስለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፤
ስለ ኀይልህም ይነጋገራሉ፤
12በዚህም ብርቱ ሥራህን፣
የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቃሉ።
13መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤
ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል።

እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤
በሥራውም
አንድ የማስሬቲክ ቅጅ፣ የሙት ባሕር ጥቅልሎች እና ሱርስት (የሰብዓ ሊቃናትን ትርጕም ይመ) እንዲሁም አብዛኛው የማስሬቲክ ቅጆች የ13 ሁለት ስንኞች የሏቸውም።
ሁሉ ቸር ነው።
14 እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤
የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።
15የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤
አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።
16አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤
የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

17 እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣
በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
18 እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣
በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
19ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤
ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።
20 እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤
ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

21አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤
ፍጡር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ቅዱስ ስሙን ይባርክ።
Copyright information for AmhNASV