Song of Solomon 4

ሙሽራው

1ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ!
እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ
ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ
እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤
ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣
የፍየል መንጋ ነው።
2ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣
ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤
ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣
ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።
3ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤
አፍሽም ውብ ነው፤
ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጕንጮችሽ፣
ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
4ዐንገትሽ አምሮ
በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም
የተሠራውን
በላዩም የጦረኞች ጋሻዎች ሁሉ ያሉበትን፣
ሺሕ ጋሻዎች የተንጠለጠሉበትን፣
የዳዊትን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።
5ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ ሆነው የተወለዱ፣
በውብ አበቦች መካከልም የተሰማሩ፣
ሁለት የሚዳቋ ግልገሎችን ይመስላሉ።
6ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣
ጥላውም ሳይሸሽ፣
ወደ ከርቤ ተራራ፣
ወደ ዕጣኑም ኰረብታ እወጣለሁ።
7ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤
እንከንም አይወጣልሽም።

8ሙሽራዬ ሆይ፤ ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤
አዎን ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤
ከአንበሶች ዋሻ፣
ከነብሮች ተራራ፣
ከኤርሞን ራስ፣ ከሳኔር ጫፍ፣
ከአማና ዐናት ውረጂ።
9እኅቴ ሙሽራዬ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል፤
በአንድ አፍታ እይታሽ፣
ከሐብልሽም በአንዱ ዕንቍ፣
ልቤን ሰርቀሽዋል።
10እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል!
ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ
የሚያረካ ነው፤
የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!
11ሙሽራዬ ሆይ፤ ከንፈሮችሽ የማር ወለላ ያንጠባጥባሉ፤
ከአንደበትሽም ወተትና ማር
ይፈልቃል፤
የልብስሽም መዐዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።
12እኅቴ ሙሽራዬ፤ የታጠረ የአትክልት ቦታ፣
ዙሪያውን የተከበበ ምንጭ፣ የታተመም ፏፏቴ ነሽ።

13ተክልሽ ሮማን፣
ምርጥ ፍሬዎች፣
ሄናና ናርዶስ ያሉበት ነው።
14እንዲሁም ናርዶስና ቀጋ፣
ጠጅ ሣርና ቀረፋ፣
የተለያዩ የዕጣን ዛፎች፣
ከርቤና እሬት፣
ምርጥ ቅመሞች ሁሉ አሉበት።
15አንቺ
ወይም እኔ ሙሽራዪቱ የተናገረችው
የአትክልት ቦታ ፏፏቴ፣
ከሊባኖስ የሚወርድ፣
የፈሳሽ ውሃ ጕድጓድ ነሽ።
ሙሽራዪቱ

16የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤
የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና!
መዐዛው ያውድ ዘንድ፣
በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤
ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤
ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።
Copyright information for AmhNASV