1 Chronicles 23

ሌዋውያን

1ዳዊት በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

2እንዲሁም መላውን የእስራኤልን መሪዎች፣ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ። 3ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቊጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ። 4ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህ  የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቈጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤ 5አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ  እግዚአብሔርን ያመስግኑ”።

6ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።

ጌድሶናውያን


7 ከጌድሶናውያን ወገን፤
ለአዳን፣ ሰሜኢ።

8 የለአዳን ወንዶች ልጆች፤
የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

9 የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤
ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።

10 የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤
ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤ እነዚህ
አራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው።
11የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ
አንድ የዕብራይስጥ ቅጅ፣ የሰብዓ ሊቃናትና የቩልጌት ትርጒሞች (እንዲሁም ቍጥር 11 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ዚና ይላሉ።
ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቈጠሩት በሥራ መደብ እንደ አንድ ቤተ ሰብ ሆነው ነው።

ቀዓታውያን


12 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤
እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ ባጠቃላይ አራት ናቸው።

13 የእንበረም ወንዶች ልጆች፤
አሮን፣ ሙሴ።
አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣  በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።
14  የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።

15 የሙሴ ወንዶች ልጆች፤
ጌርሳም፣ አልዓዛር።

16 የጌርሳም ዘሮች፤
ሱባኤል።

17 የአልዓዛር ዘሮች፤
የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።
አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።

18 የይስዓር ወንዶች ልጆች፤
የመጀመሪያው ሰሎሚት።

19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤
የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።

20 የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤
የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።

ሜራሪያውያን


21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤
ሞሖሊ፣ ሙሲ።
የሞሐሊ ወንዶች ልጆች፤
አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።
22አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።

23 የሙሲ ወንዶች ልጆች፤
ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

24እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው  በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ። 25ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በኢየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤ 26ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።” 27ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቈጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።

28የሌዋውያኑ ተግባር  በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት የአሮንን ዘሮች መርዳት፣ የቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎችን ሁሉ ማንጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ነበር። 29እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀርበውን ኅብስተ ገጽ፣ የእህል ቍርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፈረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኀላፊነት የሚቈጣጠሩ እነርሱ ነበሩ። 30በየዕለቱም  እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆሙ ነበር፤ ይህንንም ማታ ማታ 31እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ ይፈጽሙ ነበር፤ በተወሰነላቸው ቊጥርና በተሰጠውም መመሪያ መሠረት ዘወትር  በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።

32ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኛው ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው  ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኀላፊነት ያከናውኑ ነበር።
Copyright information for AmhNASV