Isaiah 12
የውዳሴ መዝሙር
1በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤
ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።
2 እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ ነው፤
እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤
▼
▼ እግዚአብሔር በሚለው ስም ፈንታ ተተክቶ የገባ ነው።
ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ድነቴም ሆኖአል።”
3 ከድነቴ ምንጮች
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
4በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
5 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና፤
ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።
6 የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤
በደስታም ዘምሩ፤
በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።
Copyright information for
AmhNASV