Numbers 13

ከነዓንን መሰለል

1  እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።”

3ስለዚህ ሙሴ  በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤ 4ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፤
5ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፤
6ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፤
7ከይሳኮር ነገድ፣ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፤
8ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፤
9ከብንያም ነገድ፣ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤
10ከዛብሎን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤

11 ከምናሴ ነገድ ይህም የዮሴፍ ነገድ
ነው፤ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤
12ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤
13ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤
14ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፤

15 ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል።

16እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።

17ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ነጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ። 18ምድሪቱ ምን እንደምትመስልና የሚኖሩባትም ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፣ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች መሆናቸውን እዩ። 19የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ? 20ዐፈሩስ እንዴት ያለ ነው? ለም ወይስ ደረቅ? ደናም ወይስ ደን አልባ? በተቻለ መጠን ከምድሪቱ ፍሬ ይዛችሁ ኑ። ወቅቱ የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር።

21ስለዚህ ወጥተው ከጺን ምድረ በዳ አንሥቶ በሌቦ
ወይም በከተማዋ መግቢያ በኩል
ሐማት በኩል እስከ ረአብ ድረስ ዘልቀው ምድሪቱን አጠኑ።
22በኔጌብ በኩል አልፈው አኪመን፣ ሴሲና ተላሚ የተባሉ የዔናቅ ዝርያዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን መጡ። ኬብሮን የተመሠረተችው ጣኔዎስ በግብፅ ምድር ከመቈርቈሯ ሰባት ዓመት አስቀድሞ ነበር። 23ወደ ኤሽኮል
ዘለላ ማለት ነው።
ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ይህንንም ከሮማንና ከበለስ ጋር በመሎጊያ አድርገው ለሁለት ተሸከሙት።
24እስራኤላውያን የወይን ዘለላ ስለ ቈረጡባትም ያች ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተባለች። 25ምድሪቱንም አሥሠው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ።

ሰላዮቹ ያቀረቡት የአሠሣ ውጤት

26ሰዎቹም፣ ሙሴና አሮን መላውም የእስራኤላውያን ማኅብረ ሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረ በዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ ተመለሱ፤ ያዩትንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ አስረዱ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። 27ለሙሴም እንዲህ ብለው ነገሩት፤ “ወደ ላክኸን ምድር ዘልቀን ገባን፤ ማርና ወተት የምታፈስስ ናት፤ ፍሬዋም ይኸው። 28በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ግን ኀያላን ሲሆኑ፣ ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፤ እንዲያውም የዔናቅን ዝርያዎች በዚያ አይተናል። 29አማሌቃውያን የሚኖሩት በኔጌብ፣ ኬጢያውያን ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በኰረብታማው አገር፣ ከነዓናውያን የሚኖሩት ደግሞ በባሕሩ አቅራቢያና በዮርዳኖስ ዳርቻ ነው።”

30ከዚያም ካሌብ ሕዝቡን በሙሴ ፊት ጸጥ አሰኝቶ፣ “እንውሓ! ምድራቸውን እንውረስ፤ ማሸነፍም እንችላለን” አላቸው።

31ከእነርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን፣ “ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ፣ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሉ። 32እነዚህም ስለ ሰለሏት ምድር በእስራኤላውያን መካከል እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አሠራጩ፤ “ያየናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ግዙፎች ናቸው፤ 33ኔፊሊምንም በዚያ አይተናል፤ የዔናቅ ዝርያዎች የመጡት ከኔፊሊም ነው። ራሳችንን ስናየው እንደ አንበጣ ነበርን፤ በእነርሱ ዐይን የታየነውም በዚሁ መልክ ነበር።
Copyright information for AmhNASV