Psalms 127
በእግዚአብሔር መታመን
የሰሎሞን መዝሙረ መዓርግ
1 እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣
ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤
እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣
ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2 የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣
ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣
አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤
እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና። ▼
▼ ወይም ተኝተው ሳሉ ምግብ ያዘጋጅላቸዋል።
3 እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤
የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
4 በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣
በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
5 ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣
የተባረከ ሰው ነው፤
ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟ
ገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።
Copyright information for
AmhNASV