Psalms 116

ምስጋና


1 የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና፣
 እግዚአብሔርን ወደድሁት።

2 ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና፣
በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።


3 የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤
የሲኦልም
ዕብራይስጡ ሲኦል ይላል።
ጣር አገኘኝ፤
ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።

4 እኔም  የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤
 እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።


5  እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤
አምላካችን መሓሪ ነው።

6  እግዚአብሔር ገሮችን ይጠብቃል፤
እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።


7 ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤
 እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤


8 አንተ ነፍሴን ከሞት፣
ዐይኔን ከእንባ፣
እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።

9 እኔም በሕያዋን ምድር፣
 በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።


10 “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣
ወይም ያኔ እንኳን

እምነቴን ጠብቄአለሁ።

11 ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣
“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።


12 ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣
 ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?


13 የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤
 የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣
ስእለቴን  ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።


15 የቅዱሳኑ ሞት፣
 በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።

16  እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤
እኔ የሴት ባሪያህ
ታማኝ አገልጋይህ ወይም ታማኝ ልጅህ
ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣
ከእስራቴም ፈታኸኝ።


17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤
 የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣
ስእለቴን  ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤

19 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣
 በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ።

ሃሌ ሉያ።
አንዳንዶች እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

Copyright information for AmhNASV