Psalms 133
የወንድማማች ፍቅር
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ
1 ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣
እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!
2 በራስ ላይ ፈሶ፣
እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣
እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣
እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው።
3 ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣
እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤
በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣
ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአልና።