Psalms 149

የድል መዝሙር


1 ሃሌ ሉያ።
አንዳንዶች ከቍ 9 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

 ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤
ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።


2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤
የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።
3ስሙን በሽብሰባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።

4  እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤
የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።

5 ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤
በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።


6 የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣
ባለ ሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤

7 በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤
ሰዎችንም ይቀጣሉ፤

8 ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣
መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤

9 ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው።
ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት።

ሃሌ ሉያ።
Copyright information for AmhNASV