Psalms 15
የእግዚአብሔር ቤተኛ
የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል?
2 አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣
ጽድቅን የሚያደርግ፤
ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
3 በምላሱ የማይሸነግል፤
በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤
ወዳጁን የማያማ፤
4 ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤
እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤
ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣
ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤
5 ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣
በንጹሓን ላይ ጒቦ የማይቀበል፤
እነዚህን የሚያደርግ፣
ከቶ አይናወጥም።
Copyright information for
AmhNASV