Psalms 16
እግዚአብሔር ርስቴ
የዳዊት ቅኔ
1 አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣
በከለላህ ሰውረኝ።
2 እግዚአብሔርን፣ ‘አንተ ጌታዬ ነህ፤
ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”
አልሁት።
3 በምድር ያሉ ቅዱሳን፣
ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው። ▼
▼ ወይም በምድሪቱ ላሉ አረማውያን፣ ካህናትና ደስ ለተሰኙባቸው መኳንንት ሁሉ ይህን እላለሁ
4 ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣
ሐዘናቸው ይበዛል፤
እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስም፤
ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤
5 እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤
ዕጣዬም በእጅህ ናት።
6 መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤
በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።
7 የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤
በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
8 እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤
እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9 ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤
ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
10 በሲኦል ▼
▼ ወይም በመቃብር
ውስጥ አትተወኝምና፤ቅዱስህም ▼
▼ ወይም በአንተ የታመነውን
መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ ▼
▼ ወይም ታሳውቀኛለህ
በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣
በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።
Copyright information for
AmhNASV