‏ Psalms 87

ጽዮን የሕዝቦች እናት

የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ማሕሌት።

1መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤
2 እግዚአብሔር ከያዕቆብ ማደሪያዎች ሁሉ ይልቅ፣
የጽዮንን ደጆች ይወድዳል።

3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤
ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ
4“ከሚያውቁኝ መካከል፣
ረዓብንና ▼
▼የግብፅ ቅኔያዊ ስያሜ ነው።
ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤
እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር፣ ▼
▼ወይም ረዓብ ባቢሎን፣ ፍልስጥኤምና ኢትዮጵያ

‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”
5በርግጥም ስለ ጽዮን፣
“ይህም ያም ሰው በእርሷ ውስጥ ተወለዱ፤
ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።
6 እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣
“ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ

7የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣
“ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።
Copyright information for AmhNASV