‏ Jeremiah 42

1የቃሬያን ልጅ ዮሐናንና የሆሻያን ልጅ ያእዛንያን
የዕብራይስጡና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (43፥2 ይመ) አዛርያ ይላሉ።
ጨምሮ፣ የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው፣
2ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። 3አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግረን ጸልይልን።”

4ነቢዩ ኤርምያስም፣ “ሰምቻችኋለሁ፤ እንዳላችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በርግጥ እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔር ያለኝን ሁሉ አንዳች ሳላስቀር እነግራችኋለሁ” አላቸው።

5እነርሱም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “እግዚአብሔር አምላክህ በአንተ በኩል የሚለውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣ እግዚአብሔር ራሱ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን። 6አምላካችንን እግዚአብሔርን በመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንታዘዛለን።”

7ከዐሥር ቀን በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 8ስለዚህ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንንና፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጠርቶ፤ 9እንዲህ አላቸው፤ “ልመናችሁን በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 10‘ባመጣሁባችሁ ጥፋት ዐዝኛለሁና፣ በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም። 11አሁን የሚያስፈራችሁን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ ይላል እግዚአብሔር 12እርሱ እንዲምራችሁና ወደ አገራችሁ እንዲመልሳችሁ እኔ እምራችኋለሁ።’

13“እናንተ ግን፤ ‘በዚህች ምድር አንቀመጥም’ ብትሉና አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባትታዘዙ፣ 14ደግሞም፣ ‘ጦርነት ወደማናይበት፣ የመለከት ድምፅ ወደማንሰማበትና ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር ሄደን በዚያ እንኖራለን’ ብትሉ፣ 15እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብፅ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣ 16የፈራችሁት ሰይፍ በዚያ ያገኛችኋል፤ የሠጋችሁበት ራብ እስከ ግብፅ ድረስ ተከትሏችሁ ይመጣል፤ በዚያም ትሞታላችሁ። 17በዚያም ለመኖር ወደ ግብፅ ለመሄድ የወሰኑ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር በርግጥ ይሞታሉ፤ ከማመጣባቸውም ጥፋት አንድ እንኳ የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይገኝም።’ 18የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ በእናንተ ላይ ይፈስሳል፤ እናንተም የመነቀፊያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ትሆናላችሁ፤ ይህንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩም።’

19“እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ እግዚአብሔር፤ ‘ወደ ግብፅ አትሂዱ’ ብሏችኋል፤ እኔም ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በርግጥ ዕወቁ፤ 20‘ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተት
ወይም በልባችሁ ስሕተት ሠራችሁ
ፈጸማችሁ።
21እነሆ፤ ዛሬ በግልጥ ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ልኮኝ የነገርኋችሁን ሁሉ አሁንም አልታዘዛችሁም፤ 22እንግዲህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በርግጥ ዕወቁ።”

Copyright information for AmhNASV