Numbers 31
ምድያማውያንን መበቀል
1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ 2“ለእስራኤላውያን ምድያማውያንን ተበቀልላቸው፤ ከዚያም ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ” አለው።3ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ምድያማውያንን ለመውጋት እንዲሄዱና ስለ እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲበቀሏቸው ከሰዎቻችሁ ጥቂቶቹን ለጦርነት አዘጋጁ። 4ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።” 5ስለዚህ ከእስራኤል ጐሣዎች ተወጣጥቶ ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሺሕ፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰው ለጦርነት ተዘጋጀ። 6ሙሴም የቤተ መቅደሱን ንዋየ ቅድሳትና ምልክት መስጫ የሆኑትን መለከቶች ከያዘው ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ከየነገዱ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነት ላከ።
7 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋር ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤ 8ከተገደሉትም መካከል አምስቱ የምድያም ነገሥታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ ይገኙባቸዋል፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በሰይፍ ገደሉት። 9ከዚያም እስራኤላውያን የምድያማውያንን ሴቶችና ሕፃናት ማረኩ፤ የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ሁሉ ነዱ፤ ሀብታቸውንም በሙሉ ወሰዱ። 10ምድያማውያኑ የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም በሙሉ አቃጠሉ። 11ሰውና እንስሳትን ጨምሮ የማረኩትንና የዘረፉትን ሁሉ እንዳለ አጋዙት። 12የማረኳቸውን ሰዎች፣ የነዷቸውን እንስሳትና የዘረፉትን ሀብት በሙሉ፣ ከኢያሪኮ ▼
▼በዕብራይስጥ የኢያሪኮ ዮርዳኖስ ማለት ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት ስም ሳይሆን አይቀርም።
ማዶ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ፣ በሞዓብ ወዳለው፣ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር እንዲሁም መላው የእስራኤላውያን ማኅበር ወዳሉበት ሰፈራቸው አመጧቸው። 13ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረ ሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ። 14ሙሴም ከጦርነት በተመለሱት በሰራዊቱ አዛዦች፣ ማለትም በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።
15እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ሴቶችን ሁሉ እንዴት በሕይወት ትተዉአቸዋላችሁ?” 16የበለዓምን ምክር ተቀብለው በፌጎር በተፈጸመው ድርጊት እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲመለሱና የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ሕዝብ እንዲቀሠፍ ያደረጉት እነርሱ ናቸው። 17አሁንም ወንዶቹን ልጆች ሁሉ፣ ወንድ ያወቍትንም ሴቶች በሙሉ ግደሏቸው፤ 18ነገር ግን ወንድ ያላወቁትን ልጃገረዶች ሁሉ ለራሳችሁ አስቀሯቸው።
19“ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም የተገደለውን የነካ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ይቈይ። በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና ምርኮኞቻችሁን አንጹ። 20ማናቸውንም ልብስ እንዲሁም ከቈዳ፣ ከፍየል ጠጕር ወይም ከዕንጨት የተሠራ ማንኛውንም ነገር አንጹ።”
21ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ የሰጠው የሕጉ ሥርዐት ይህ ነው፤ 22ወርቅ፣ ብር፣ ናስ፣ ብረት፣ ቈርቈሮ፣ እርሳስ 23እንዲሁም እሳትን መቋቋም የሚችል ማንኛውም ነገር በእሳት ውስጥ ማለፍ አለበት፤ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል፤ ይህም ሆኖ መንጻት አለበት። እሳትን መቋቋም የማይችል ማንኛውም ነገር በዚሁ ውሃ ውስጥ ማለፍ አለበት። 24በሰባተኛው ቀን ልብሳችሁን ዕጠቡ፤ ትነጻላችሁም፤ ከዚያም ወደ ሰፈር መግባት ትችላላችሁ።”
ምርኮን መከፋፈል
25 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 26“አንተ፣ ካህኑ አልዓዛርና በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ያሉት የየቤተ ሰቡ አለቆች ሆናችሁ የተማረከውን ሕዝብና እንስሳት ሁሉ ቍጠሩ። 27ምርኮውንም ለሁለት ከፍላችሁ በጦርነቱ ለተካፈሉት ወታደሮችና ለቀረው ማኅበረ ሰብ አከፋፍሉት። 28በጦርነቱ ከተካፈሉት ወታደሮች ድርሻ ላይ፣ ከሰውም ሆነ ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ ወይም ከፍየል ከየአምስት መቶው አንዱን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ግብር አውጣ። 29ይህንም ግብር ከድርሻቸው ላይ ወስደህ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ፈንታ በማድረግ ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው። 30ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ደግሞ ከሰውም ይሁን ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ፣ ከፍየል ወይም ከሌሎች እንስሳት ከየአምሳው አንዳንድ መርጠህ፣ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ስጣቸው።” 31ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። 32ወታደሮቹ ማርከው ከወሰዱለት ምርኮ ውስጥ የቀረው ይህ ነበር፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺሕ በግ፣ 33ሰባ ሁለት ሺሕ የቀንድ ከብት፣ 34ስድሳ አንድ ሺሕ አህያ 35ወንድ ያላወቁ ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሴቶች።36በጦርነቱ ላይ የነበሩት ወታደሮች እኩሌታ ድርሻ ይህ ነበር፤
ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺሕ አምስት መቶ በግ፣ 37ከእነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠ ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበር።
38ሠላሳ ስድስት ሺሕ የቀንድ ከብት፣ ከእነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሰባ ሁለት ነበር።
39ሠላሳ ሺሕ አምስት መቶ አህያ፣ ከእነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ስድሳ አንድ ነበር።
40ዐሥራ ስድስት ሺሕ ሰው፣ ከእነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሠላሳ ሁለት ነበር።
41ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የሆነውን ግብር ለአልዓዛር ሰጠው።
42ሙሴ ከዘመቱት ሰዎች የለየው የእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ማለትም፣ 43የማኅበረ ሰቡ ድርሻ ይህ ነበር፤ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺሕ አምስት መቶ በግ፣ 44ሠላሳ ስድስት ሺሕ የቀንድ ከብት፣ 45ሠላሳ ሺሕ አምስት መቶ አህያ፣ 46ዐሥራ ስድስት ሺሕ ሰው። 47ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ላይ፣ ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ከየአምሳው ሰውና እንስሳ አንዳንድ መርጦ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጣቸው።
48ከዚያም በኋላ በሰራዊቱ ክፍሎች ላይ የተሾሙት የሻለቆችና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ ቀርበው፣ 49እንዲህ አሉት፤ “እኛ አገልጋዮችህ በእጃችን ሥር ያሉትን ወታደሮች ቈጥረናል፤ አንድም የጐደለ የለም። 50ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የእግር ዐልቦዎች፣ የእጅ አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጕትቻዎችና የዐንገት ሐብሎች በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ማስተስረያ እንዲሆነን መባ አድርገን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አምጥተናል።”
51ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ የተሠራውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሏቸው። 52ሙሴና አልዓዛር ከሻለቆቹና ከመቶ አለቆቹ በመቀበል ስጦታ አድርገው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቀረቡት ወርቅ ዐሥራ ስድስት ሺሕ ሰባት መቶ አምሳ ሰቅል ▼
▼አንድ መቶ ዘጠና ኪሎ ግራም ያህል ነው።
መዘነ። 53እያንዳንዱም ወታደር ለራሱ የወሰደው ምርኮ ነበረው። 54ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሻለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለእስራኤላውያን መታሰቢያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡት።
Copyright information for
AmhNASV